Fana: At a Speed of Life!

የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ተሳታፊ ሀገራት አዲስ አበባ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ተሳታፊ ሀገራት አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

ከተሳታፊ ሀገራት መካከል የብሩንዲ፣ የደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ከ17 ዓመት ብሔራዊ ቡድኖች ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በሴካፋ የእግር ኳስ ውድድር በምድብ አንድ÷ ኢትዮጵያ፣ ታንዛንያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ብሩንዲ በምድብ ሁለት የተደለደሉ ሀገራት ናቸው።

ይሁን እንጅ ከተሳታፊ ሀገራት መካከል ኤርትራ እና ሩዋንዳ ከበጀት ጋር በተያያዘ ችግር ምክንያት ከውድድሩ እራሳቸውን ማግለላቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል::

በውድድሩ አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡ ብሔራዊ ቡድኖች የሴካፋ ዞንን ወክለው በአልጄሪያ በጥር ወር 2015 ዓ.ም በሚካሄደው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ሻምፒዮና ይሳተፋሉ።

ውድድሩ ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል።
በሁለት ምድብ ተከፍሎ በሚካሄደው ውድድር ኢትዮጵያን ጨምር 10 ሀገራት ይሳተፋሉ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.