ዓለምአቀፋዊ ዜና

አራት ግዛቶች ሩሲያን ለመቀላቀል ውሳኔ አሳለፉ

By Alemayehu Geremew

September 28, 2022

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶኔስክ፣ ሉሃንስክ፣ ኬርሶን እና በደቡባዊ ዩክሬን የምትገኘው ዛፖሮዢያ ወደ ሩሲያ መጠቃለል እንደሚፈልጉ ባካሄዱት ሕዝበ ውሳኔ አረጋግጠዋል፡፡

በሉሃንስክ የተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ ቆጠራ የተጠናቀቀ ሲሆን ከ98 በመቶ በላይ የሚሆኑት ነዋሪዎች ወደ ሩሲያ መጠቃለል እንደሚፈልጉ መወሰናቸውን ተገልጿል።

በተመሳሳይ ከ99 በመቶ በላይ የሚሆኑት ዶኔስካውያንም ወደ ሩሲያ መጠቃለል እንደሚፈልጉ ከድምፅ ቆጠራው ውጤት ማወቅ ተችሏል ነው የተባለው፡፡

ዛፖሮዢያ እና ኬርሶንም በተከታታይ 93 እና 87 በመቶ በሆነ ድምፅ ከዩክሬን ተነጥለው ከሩሲያ ጋር መዋሃድ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡

አሁን የመጡትን አዲስ ክልሎች ወደ ሩሲያ ለማካለል የፓርላማውን እና የፕሬዚዳት ቭላድሚር ፑቲንን ይሁንታ ማግኘት እንዳለበት አር ቲ ዘግቧል፡፡

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ውሳኔው የብዙኃኑ ስለሆነ ሁሉም ነገር በፍጥነት እንደሚፈጸም ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።