Fana: At a Speed of Life!

የአለርጂ ሳይነስን ለማስታገስ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለርጂ ሳይነስ በአፍንጫ ሰርን፣ በአይን መካከል እና ግምባር ውስጥ የሚገኙ ህብረ ህዋሳት በሚያብጡበት ጊዜ የሚፈጠር ህመም ነው፡፡

ህመሙ የአፍንጫ ውስጠኛ ክፍል እርጥበት እንዲይዝ በማድረግ አፍንጫ በተፈጥሮ ከአቧራ፣ ከብክለት እና ከበሺታ አምጭ ህዋሳት የሚያደርገውን የመከላከል አቅም በመቀነስ የአተነፋፈስ ችግር እንደሚፈጥር የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

የሳይነስ ምልክቶችም የፊት ህመም ወይም መወጠር፣ የአፍንጫ መርጠብ፣ የማሽተት አቅም ማጣት፣ ሳል ወይም የአተነፋፈስ ችግር መሆናቸውንም ይገልጻሉ።

ህመሙን ለማስታገስም ፦

በቂ እረፍት ማድረግ፦ እረፍት መውሰድ የሰውነትን በሺታ እና ህመም የመከላከል አቅም እንዲጨምርና በፍጥነት እንዲያገግም ይረዳል።

ፈሳሽ በብዛት መውሰ፦ እንደ ህክምነናባለሙያዎች ገለጻ ፈሳሽ በብዛት መውሰድ በሰውነት ውስጥ የሚመነጩ እና ሳይነሶችን የሚደፍኑ ወፍራም ፈሳሾች እንዲቀጥኑ በመድረግ ህመሙን መከላከል ያስችላል።

አልኮል መጠጣት በሳይነሶቻችን አካባቢ እብጠት እንዲኖር በማድረግ ህመሙን የሚያባብስ ሲሆን አልኮልና አነቃቂ (ካፌን) የበዛባቸውን መጠጦች አለመጠቀምም ይመከራል።

የሞቀ ውሃ አፍንጫ ላይ መያዝ፦ የሞቀ ውሀ ውስጥ የተነከረ ፎጣ በአፍንጫ አካባቢ እና በላይኛው ጉንጭ ላይ በማድረግ ፊት አካባቢ የሚሰማን ህመም ማስታገስ እንደሚቻል ሜዲካ ዌብ እና ኸልዝ ላይን መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ባለፈም አፍንጫን በሚገባ ማፅዳት፣ በሞቀ ውሃ መታጠን፣ ከጭንቅላት ቀና ብሎ መተኛት ሳይነስን ለመከላከል ይረዳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.