Fana: At a Speed of Life!

ለ10 ተንቀሳቃሽ የህክምና ክሊኒኮች የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ 10 ተንቀሳቃሽ የህክምና ክሊኒኮች ድጋፍ ማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ተፈራረመ።

 

የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ሰመሬታ ሰዋሰው ተፈራርመዋል።

 

በድጋፍ ስምምነቱ መሠረትም የጃፓን መንግስት 185 ሚሊየን ብር የሚያወጡ 10 ተንቀሳቃሽ የህክምና ክሊኒኮችን እንደሚያበረክት ተገልጿል።

 

ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮቹ ሙሉ የህክምና አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎችን የሚያሟሉ መሆናቸው ተመላክቷል።

 

ክሊኒኮቹ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለሚገኙ አርብቶ አደሮች እና በተለያዩ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑም ተጠቁሟል።

 

በድጋፍ ስምምነቱ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.