ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እንግሊዝ የግብር ቅነሳ ዕቅዶቿን በድጋሚ እንድታጤን ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የእንግሊዝ መንግሥት የግብር ቅነሳ ዕቅዶቹን በድጋሚ እንዲያጤን አሳስቧል፡፡
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የእንግሊዝ መንግስት በዘርፉ የሚወስዳቸው እርምጃዎች በኃይል አቅርቦት ቀውስ እና በዋጋ ንረት ክፉኛ የተጎዱ ቤተሰቦችን ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸው ጠቁሟል፡፡
ድርጅቱ በእንግሊዝ የግብር ቅነሳ እቅዶች ላይ ከባድ ነቀፌታ የሰነዘረ ሲሆን÷ የሊዝ ትረስ መንግስት የእኩልነት ተጠቃሚነት ችግር እንዳይፈጠር የሚውጡ ዕቅዶችን በድጋሚ እንዲያጤን ጠይቋል።
መቀመጫውን ዋሺንግተን ያደረገው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የክዋሲ ኩዋርቴንግ አነስተኛ በጀት የእንግሊዝ ባንክ በኑሮ ውድነት ላይ የዋጋ ንረትን ለመቅረፍ የሚያደርገውን ጥረት አደጋ ላይ ጥሏል ሲል ትችት ሰንዝሯል፡፡
በፈረንጆቹ በህዳር 23 በኳርቴንግ የቀረበው ዕቅድ “የእንግሊዝ መንግስት የሚገባቸው አካላትን የበለጠ ያነጣጠረ ድጋፍ ለመስጠት እና የታክስ እርምጃዎችን በተለይም ከፍተኛ ገቢ ያገኙ ሰዎች የሚጠቅሙበትን መንገድ እንዲቃኝ እድሉን ያቀረበ ነበር ብሏል።
ትችቱ የመጣው የእንግሊዙ ቻንስለር ክዋሲ ኳርቴንግ ÷ ባለፈው ዓርብ ቃል ከተገባው የ45 ቢሊየን ፓውንድ የግብር ቅናሽ በተጨማሪ ሌሎች የግብር ማስተካከያዎች እንደሚያደረጉ መናገራቸውን ተከትሎ መሆኑን የዘጋርዲያን ዘገባ አመላክቷል ፡