ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሶማሌያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ ኢመደአን ጎበኙ

By Mikias Ayele

September 28, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሀሙድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደርን (ኢመደአ) ጎበኙ።

በዕለቱ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ለፕሬዚዳንቱና ልዑካቸው አቀባበል አድርገውላቸወዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ የአስተዳደሩን የዲጂታል ኤግዚቢሽን እና የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን ለእንግዶቹ አስጎብኝተዋል፡፡