Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን እንደሚከበር ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
 
በዓሉ በዛሬው ዕለት በመላው አዲስ አበባ በፓናል ውይይቶችና አውደርዕይ መከፈቱም ነው የተገለጸው፡፡
 
በነገው ዕለት በክፍለ ከተማ ደረጃ የፓናል ውይይት የሚደረግ ሲሆን÷ መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም በማዕከል ደረጃ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመቀናጀት የማጠቃለያ ፓናል ውይይት ይካሄዳል ተብሏል፡፡
 
መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባበር በአባገዳዎች ብቻ እየተመራ የሚካሄድ እንደሆነ መገለጹን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የወንድማማችነት፣ እህትማማችነትና የምስጋና በዓል የሆነው ኢሬቻ “የኦሮሞ ህዝብ የጨለማውን ጊዜ አሳልፈን ብርሃን ያሳየኸንን ፈጣሪ እናመሰግናለን፤ መሬቱን አረጠብክልን፤ ውሃው ሞላ፤ የደፈረሰው ጠራልን እናመሰግናለን” በማለት ለፈጣሪው ምስጋናውን የሚያቀርብበት በዓል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.