የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

By Meseret Awoke

September 28, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ታዋቂው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ገና በአፍላ ዕድሜ ላይ እያለ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ በጣም አዝኛለሁ ብለዋል፡፡

ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትንና ብርታትን እመኛለሁም ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!