Fana: At a Speed of Life!

የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች በግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉ የእርድ ሰንጋ፣ ለስላሳ መጠጦችንና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁስ ያካተተ ነው፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊና የድጋፋ አሰባሳቢ ዮናስ መላኩ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት÷ አሸባሪው ህወሓትን እየመከተ ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ለአራተኛ ዙር ያመጣነው ድጋፍ ከከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎች የተሰበሰበ ነው፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ጋሻው አስማሜ ድጋፉን በተረከበቡበት ወቅት እንደገለጹት÷ በግንባር ለተሰለፈው መከላከያ ሠራዊት የተደረገው ድጋፍ አስፈላጊ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.