Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ይፈጸማል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተወዳጁ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚፈጸም የቀብር ሥነ ስርዓቱን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የቀብር ሥነ ስርአቱ ነገ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀምም ነው ኮሚቴው የገለጸው፡፡

የቀብር ሥነ ስርዓቱን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ በአርቲስቱ መኖሪያ ቤት በሰጠው መግለጫ÷ ነገ በአርቲስቱ መኖሪያ ቤት እንዲሁም በወዳጅነት ፓርክ ከ6 ሰዓት ጀምሮ በመንግሥት ኃላፊዎች፣ በሙያ አጋሮቹ፣ በአድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ የአስክሬን ስንብት እንደሚካሄድ ገልጿል።

ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸምም ተናግሯል።

አርቲስት ማዲንጎ በትላንትናው ዕለት በድንገተኛ ህመም በህክምና ላይ እያለ ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

ከአርቲስቱ ህልፈት ጋር ተያይዞ እየወጡ የሚገኙ ሀሰተኛ መረጃዎችን ወደጎን በመተው ለአርቲስቱ ያለንን ክብር እናሳይ ሲልም የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ መልዕክት አስተላልፏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.