Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ ባዛርና ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአራት ቀናት የሚቆይ የኢሬቻ ባዛርና ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ከተማ ተከፈተ፡፡

በመጪው ቅዳሜና እሁድ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን ባዛርና ዐውደ ርዕይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፍተዋል።

ከንቲባ አዳነች በዚሁ ወቅት አዲስ አበባ ከተማ የኅብረ ብሔራዊነት እና የወንድማማችነት ምልክት መሆኗ ን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የመዲናዋ ነዋሪዎች ሃይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓላትን በጋራ በማክበር አንድነታቸውን ይበልጥ እያጠናከሩ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ኢሬቻ የሰላም፣ የወንድማማችነትና የምስጋና በዓል መሆኑን የተናገሩት ከንቲባዋ አዳነች፥ በዓሉን ወንድማማችነትንና አንድነትን መሰረት ባደረገ መልኩ በጋራ ልናከብረው ይገባል ነው ያሉት፡፡

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ በበኩላቸው ፥ ኢትዮጵያ ያላት ብዝሃ ባህልና እሴቶች የአብሮነታችን መገለጫዎች ናቸው ብለዋል።

እነዚህን ሃብቶቻችንን ጠብቀን ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነት አለብን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በባዛርና ዐውደ ርዕዩ የተለያዩ ባህላዊ አልባሳት ለገበያ የቀረቡ ሲሆን ፥ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች በወረዳ ደረጃ መከፈቱንም ነው የገለጹት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.