Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ችግር ፈቺ ሀሳብ ባላቸው ልጆቿ እድገቷን ታስቀጥላለች – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ችግር ፈቺ ሀሳብ ባላቸው ልጆቿ እድገቷን ታስቀጥላለች ሲሉ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሯ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ታለንት ልማት ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡

ጉብኝታቸውን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸውን አስታውሰዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ታለንት ልማት ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ዙር 1 ሺህ የፈጠራና የተግባር ትምህርት ፍላጎት ያላቸውን ባለ ልዩ ተሰጥዖ ዜጎች ከመላው ኢትዮጵያ ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተገንዝበናል ብለዋል።

ይህ የነገይቱን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎች ዘርፍ ወደፊት የሚያራምዱ እንቁ ሃሳብ አፍላቂ ዜጎች ሀሳባቸውን ወደ ተግባር የሚቀይሩበት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ለበርካታ ኢንተርፕራይዞች እና የወደፊት ትላልቅ ኩባንያዎች መፈጠሪያ መሰረት ሆኖ የሚያገልግል እንዲሁም ለብዙዎች የስራ እድል መፈጠር በር የሚከፍት ኢንስቲትዩት እንደሚሆን ያላቸውን እምነትም ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ችግር ፈቺ ሀሳብ ባላቸው ልጆቿ እድገቷን  ታስቀጥላለች ያሉት ሚኒስትሯ ይህን ተቋም ዓለም ከደረሰበት የፈጠራ ስራዎች የልህቀት ማማ ለማድረስ ሀሳብ ላፈለቁ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.