በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ በድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ህልፈት የተሰማውን ሐዘን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ በድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ህልፈት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቪግኒ ተርኪን ÷ በታዋቂው ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ህልፈት በራሳቸው እና በኤምባሲው ሰራተኞች ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡
ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከድምጻዊነቱ ባሻገር ሀገር ወዳድ ዜጋ እንደነበርም ነው አምባሳደሩ ያወሱት፡፡
ድምጻዊው በስራዎቹ ግንባር ላይ የሚገኘውን መከላከያ ሰራዊትን ሲያነቃቃ እና ሲያበረታታ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የሀገር ኩራት እንደነበር የገለጹት አምባሳደር ኢቪግኒ ተርኪን÷ የድምጻዊው ህልፈት ለኢትያውያን ትልቅ ሀዘን መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
አምባሳደሩ ለድምጻዊው ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን መመኘታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡