Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የሚገኙ የግል ጤና ተቋማት ማህበር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል የግል ጤና ተቋማት ማህበር ለመከላከያ ሰራዊት ያሰባሰበውን ግማሽ ሚሊየን ብር ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አስረክቧል።
 
አቶ ኦርዲን በድጋፍ ርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት÷በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ እየመከተ ላለው የመከላከያ ሰራዊት በክልሉ የሚገኘው ህዝብና ተቋማት ከህይወት መስዋዕትነት ጀምሮ በገንዘብ፣ ደም በመለገስ፣ በቁሳቁስና በሌሎች ዘርፎች ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡
 
ሀገርን ለማዳን በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አስተዋጽኦ የማድረግ እና እድሉን መጠቀም ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል ብለዋል።
 
የግል ህክምና ተቋማት ለህዝብ እየሰጡ ከሚገኘው አስተዋፅኦ በተጨማሪ ለሰራዊቱ ድጋፍ በማድረጋቸው ያመሰገኑት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይም ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።
 
በመተጋገዝ፣ በመደጋገፍና ወንድማማችነት በማጠናከር ሀገራችንን ማሻገር አስፈላጊ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ የግል የጤና ተቋማት የበለጠ እንዲደራጁና የክልሉ መንግስት ድጋፉን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።
 
የማህበሩ ተወካዮችም ማህበሩ ሰራዊቱን ከመደገፍ በተጨማሪ እንደ ሀገርና ክልል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተባባሰበት እና ሌሎች ሀገራዊና ክልላዊ ችግሮች በገጠሙበት ወቅት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
 
በቀጣይም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ከማጠናከርም ባሻገር ሌሎች ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ መጠቆማቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.