Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
 
የትራፊክ አደጋው ከኢንጪኒ ከተማ ወደ ሽኖ ከተማ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝባ ማመላለሻ አውቶብስ ከተሳቢ ጋር ተጋጭቶ ነው የተከሰተው፡፡
 
በተፈጠረው አደጋም የ15 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ መሆኑን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪም በ30 ሰዎች ላይ ከባድ እና በሀሉት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.