የሀገር ውስጥ ዜና

የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

By Feven Bishaw

September 28, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ቤንዚን በሊትር 57 ብር ከ05 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም እንዲሁም ኬሮሲን በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡