Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተወዳጁ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት እንደሚፈጸም የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ አስታውቋል።

የቀብር ሥነ ሥርአቱ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ነው ኮሚቴው የገለጸው፡፡

የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ ÷ በዛሬው ዕለት በአርቲስቱ መኖሪያ ቤት እንዲሁም በወዳጅነት ፓርክ ከ6 ሰዓት ጀምሮ በመንግሥት ኃላፊዎች፣ በሙያ አጋሮቹ፣ በአድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ የአስክሬን ስንብት እንደሚካሄድ ጠቁሟል።

ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮም በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ሥርዓተ ቀብሩ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከትናንት በስቲያ በድንገተኛ ህመም ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.