Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 11 ሺህ ሄክታር መሬት የበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዘንድሮው የበጋ ወራት 11 ሺህ ሄክታር መሬት የበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊው አቶ ባበክር ኻሊፋ÷ በክልሉ ለሚከናወነው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እየተደረገ ያለውን ዝግጅት በተመለከተ በባምባሲ ወረዳ ተገኝተው ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት÷ በክልሉ ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሆነ መታዘባቸውን ገልጸዋል፡፡

በተያዘው የበጋ ወራት 11 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት መታቀዱን ጠቅሰው÷ ለዚህም አስፈላጊ የዝግጅት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቢሮው ለአርሶ-አደሩ የምርጥ ዘር አቅርቦትን ጨምሮ አስፈላጊውን እገዛና ክትትል እንደሚያደርግም አመላክተዋል፡፡

በ2014/15 የመኸር ምርት ዘመን በክልሉ 8 ሺህ 622 ሔክታር መሬት በስንዴ ሠብል እንደተሸፈነ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

የባምባሲ ወረዳ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሊ መርቀኒ በበኩላቸው÷ በወረዳው ለበጋ መስኖ ልማት የመስኖ ማሳ ጽዳትን ጨምሮ ከወዲሁ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.