Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከአሜሪካ የሴኔት ደህንነት ጉዳዮች ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከአሜሪካ የሴኔት የደህንነት ጉዳዮች ሰብሳቢ ማርክ ዋርነር ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ስላለው ግጭት፣ በኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ዳያስፖራው በልማት ዘርፍ ባላቸው ሚና ዙሪያ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

ሴናተር ማርክ ዋርነር ከ2008 ጀምሮ በሴናተርነት በማገልገል ላይ ሲሆኑ ከጥር 2021 አንስቶ የሴኔቱ የደህንነት ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው በመስራት ላይ ናቸው።

በተያያዘ ዜና አምባሳደር ስለሺ በአሜሪካ ከሚኖሩ ከ200 በላይ ዳያስፖራዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አመላክተዋል።

ውይይቱ ዳያስፖራው የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነትን በማጠናከር፣ ኢትዮጵያን በመደገፍና በልማት ስራዎች እየተወጣ ያለውን ሚና በተመለከተ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

አምባሳደር ስለሺ በአሜሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ለሀገራቸው እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.