Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ አስክሬን የሽኝት መርሐግብር በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ አስክሬን ሽኝት መርሐግብር በወዳጅነት አደባባይ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

 

ከአርቲስቱ መኖሪያ ቤት ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር÷ አሁንም በወዳጅነት ፓርክ የሽኝት ስነ ስርዓቱ እንደቀጠለ ነው፡፡

 

በመቀጠልም መንግሥት ባለስልጣናት፣ በሙያ አጋሮቹ፣ በአድናቂዎቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት የአስክሬን ስንብት ይካሄዳልም ነው የተባለው፡፡

 

የስንብት መርሐግብሩ እንደተጠናቀቀም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ስነስርዓቱ እንደሚካሄድ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
ተወዳጁ የጥበብ ሰው ማዲንጎ አፈወርቅ ስለ ፍቅር፣ ትዝታ፣ ባህል፣ ሀገር፣ ታሪክና ሌሎች ጉዳዮችን የሚዳስሱ መልዕክቶችን በተስረቅራቂ ድምጹ በማዜም በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ስራ ላይ የራሱን አሻራ አሳርፏል።
ማዲንጎ አፈወርቅ ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሄድና ማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሰራ አርቲስት መሆኑም ይታወቃል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.