Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት 31 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልላዊ መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት 31 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ አስረክበዋል፡፡
ወ/ሮ ሚስራ የመከላከያ ሰራዊት አሸባሪው ህወሓት በሀገር ላይ የከፈተውን ጦርነት በመመከት የኢትዮጵያን ሰላም ለማረጋገጥ የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሐረሪ ክልል ሕዝብ ለሰራዊቱ ያለውን ደጀንነት ለማረጋገጥ 31 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል ነው ያሉት።
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ወታደር መሆኑን ገልጸው÷ የሐረሪ ክልል ሕዝብ ስላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
የአሸባሪውን ህወሓት ወረራ በመመከት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ መከላከያ ሰራዊት የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር እየከፈለ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመከላከያ ሰራዊት የሚያሳየውን ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.