Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የተካሄደው ጥናት ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰኔ 2013 እስከ ታህሳስ 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የተካሄደው ጥናት ውጤት ይፋ ሆኗል።

ጥናቱ የተካሄደው በአማራ ክልል በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽሕፈት ቤት፣ በአማራ ምሁራን መማክርት እና በአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ነው።

በጥናቱ በሕዝቡ ላይ የደረሰውን ሁለንተናዊ ጥቃትና ውድመት ማኅበረሰቡ ውስጥ ገብቶ በማጥናት መሰነድ መቻሉን የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ዋና ጸሐፊ አስማረ ደጀን ገልጸዋል።

የጥናቱ ሂደት መረጃ፦

• ጥናቱ ከሰኔ 2013 እስከ ታህሳስ 2014 ዓ.ም ያለውን ጊዜ ያካተተ ነው

• ጥናቱ 8 ዞኖችን፣ አንድ ከተማ አስተዳደር፣ 87 ወረዳዎችና 945 ቀበሌዎች ላይ ተደርጓል

• በክልሉ የደረሰው ጥፋትና ውድመቱን በግልፅ በቦታና መጠን የሚያሳይ ነው

• በጥናቱ ከ4000 በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል

• ጥልቅ ጥናት በማድረግ የችግሩን ክፋትና ስፋት የሚያሳይ ውጤት ላይ ተደርሷል

• ጥናቱ በመጽሐፍ መልክ ተዘጋጅቷል፤ በቅርቡ ለሕዝብ ይደርሳል።

አሸባሪው ሕወሃት ከሰኔ 2013 እስከ ታህሳስ 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ያደረሰው ጉዳት፦

• 292 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት አውድሟል

• 240 ሺህ 236 ሰዎች ላይ ሰብአዊ ጉዳት /ግድያ፣ ድብደባ ቀላልና ከባድ ጉዳት/ መድረሱ ተገልጧል።

• የኢትዮጵያን ወግና ባህል በማይመጥን መልኩም 29 ወንዶች ላይ የግብረ ሰዶም ተግባር ተፈፅሞባቸዋል።

ይህ ራሳቸውን አጋልጠው የቀረቡት ይሁኑ እንጂ የጥቃቱ መጠን ከዚህም ይልቃል መባሉን አሚኮ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.