Fana: At a Speed of Life!

በኡጋንዳ 6 የጤና ባለሙያዎች በኢቦላ መያዛቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ አምሥት ሐኪሞች እና አንድ የአንስቴዢያ ባለሙያ በኢቦላ ቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ፡፡

የሕክምና ባለሙያዎቹ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ለሕክምና ወደ ለይቶ ማቆያ መወሰዳቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል፡፡

የሙቤንዴ የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ግብረ-ኃይል ፣ የወረርሽኝ ዋና ማዕከል፣ የኡጋንዳ የሕክምና ማኅበር እንዲሁም ብሔራዊ የሐኪሞች ቡድን በተናጠል በሰጡት መግለጫ በሽታው ከታማሚዎች ወደ ሕክምና ባለሙያዎቹ መተላለፉን አስታውቀዋል።

የኢቦላ ቫይረስ በኡጋንዳ ሲቀሰቀስ ይህ ለአምስተኛ ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያው በጉሉ ወረዳ በፈረንጆቹ 2000 ላይ የተቀሰቀሰው ነው ተብሏል፡፡

በወቅቱ የሕክምና ቡድን መሪ የነበሩት ዶክተር ማቲው ሉክዊያ በቫይረሱ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

እንደ ኡጋንዳ ጤና ሚኒስቴር በአሁኑ ወረርሽኝ እስካሁን 24 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው የአምሥቱ ሕይወት አልፏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.