የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድሥተ ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡
ከሥርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ÷ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ዘመድ ወዳጆች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና አድናቂዎቹ በተገኙበት በመኖሪያ ቤቱ እና በወዳጅነት ዐደባባይ የአስከሬን ሽኝት ተካሂዷል፡፡
አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
ማዲንጎ አፈወርቅ የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር።
በሥርዓተ ቀብሩ ላይ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲሁም የአርቲስቱ ቤሰተቦች፣ ዘመድ ወዳጆች እና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡