Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከነገ እስከ እሁድ ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር አይቻልም

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ምክንያት ከነገ አርብ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደማይቻል ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመት ኤጀንሲ እንዳስታወቀው÷ ቅደሜ መስከረም 21 ቀን 2015 ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል በሁሉም የመዲናዋ በሮች የሚገቡ የበዓሉ ታዳሚዎች ስለሚኖሩ ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴን መገደብ አስፈልጓል።

በዚሁ መሠረት ከነገ አርብ መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ እሁድ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ.ም ማታ 12 ሰዓት ድረስ የሞተር እንቅስቃሴ በከተማዋ የተከለከለ መሆኑን ተገንዝባችሁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ሲል ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

የተጣለውን ገደብ ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድምነው ኤጀንሲው ያሳሰበው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.