Fana: At a Speed of Life!

በቤርአኖ ወረዳ 124 ሔክታር የሚያለማ የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ቤርአኖ ወረዳ 124 ሔክታር የማልማት አቅም ያለው የመስኖ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

በፌዴራል መንግሥት ወጪ የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት በቤርአኖ ወረዳ ሂሎ ኖጉድ ቀበሌ የሚኖሩ 496 ከፊል አርብቶ አደር ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

ፕሮጀክቱን በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ኢብራሂም ኡስማን የተመራ ልዑክ መርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

የሂሎ ኖጉድ ቀበሌ ነዋሪዎች የመስኖ ፕሮጀክት ለአገልግሎት በመብቃቱ ደስታቸውን ገልጸው÷ ፕሮጀክቱ የግብርና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.