የሀገር ውስጥ ዜና

በቤርአኖ ወረዳ 124 ሔክታር የሚያለማ የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ

By ዮሐንስ ደርበው

September 29, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ቤርአኖ ወረዳ 124 ሔክታር የማልማት አቅም ያለው የመስኖ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

በፌዴራል መንግሥት ወጪ የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት በቤርአኖ ወረዳ ሂሎ ኖጉድ ቀበሌ የሚኖሩ 496 ከፊል አርብቶ አደር ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡