Fana: At a Speed of Life!

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ነጋዴወች እና ባለሃብቶች ለአቅመ ደካሞች ሰደቃ ወይም ምጽዋት በመስጠት ተግባር ሊሰማሩ ይገባል ብለዋል።

የችግር ጊዜን ጠብቀው አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የእስልምና አስተምህሮ የማይፈቅደው በመሆኑ ይህን የሚያደርጉ አካላት ሊታረሙ እንደሚገባና መንግስትም እየወሰደ ያለው ህግን የማስከበር እርምጃ ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል።

የጁምዓ ሰላት እንዲሁም ህዝበ ሙስሊሙ በብዛት የሚሰበሰብባቸው ሃይማኖታዊ ስርዓቶችን አስመልክቶ በዑለማወች ተመክሮ መፍትሄ እስከሚሰጥበት ድረስ የተወሰነ ነገረ እንደሌለም ተናግረዋል።

ሆኖም ሁሉም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲደርጉ አሳስበዋል።

ወጣቶች በበጎ አድራጎት ተግባራት ተሰማርተው እያደረጉት ላለው እገዛና ጥረትም ምስጋና አቅርበዋል።

ሁሉም ወደ ፈጣሪ በመለመንና ከመጥፎ ተግባራት በመራቅ እንዲሁም የህክምና ባለሙያወችን ምክር በመስማት መተግበር እንደሚገባውም አሳስበዋል።

በመለሰ ምትኩ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.