የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የ11 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

By Amele Demsew

September 29, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በጽህፈት ቤታቸው በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ11 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ።

አምባሳደሮቸ የኢራን ፣ ቤልጂየም ፣ ኖርዌይ ፣ ኒጀር ፣ ኦስትሪያ ፣ ብራዚል፣ ኩዌት ፣ ሳኡዲ አረቢያ ፣ ፓርቹጋል ፣ ሲንጋፓር እና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ናቸው።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የሹመት ደብዳቤ ካቀረቡ አምባሳደሮች ጋር በኢትዮጵያ እና በሀገራቱ መካከል ያሉ ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።