Fana: At a Speed of Life!

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡

ሊጉ የወልቂጤ ከተማና አርባ ምንጭ ከተማ 7 ሰዓት ላይ የሚጀምር ሲሆን ፥ በተመሳሳይ ቀን ባህር ዳር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ 10 ሳዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

በሊጉን የአንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዳሜ ኢትዮጵያ መድን ከቅዱስ ጊዮርጊስ 7 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ ፥ ድሬዳዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

በሊጉ ሦስተኛው ቀን እሁድ ወላይታ ዲቻና ኢትዮጵያ ቡና 7 ሰዓት እንዲሁም ሐዋሳ ከተማና ለገጣፎ ለገዳዲ 10 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡

ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ 7 ሰዓት ሲጫወቱ ፥ መቻል እና ሀዲያ ሆሳዕና 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ከቤትኪንግ ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.