Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትስስር እና ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትስስር እና ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የጋራ ስምምነትን ይፋ አድርጓል።

ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ከሀገራቱ ከተውጣጣ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል።

መሪዎቹ በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሉባቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ማድረጋቸውን እንዲሁም የሽብርተኝነት እና የፅንፈኝነት ስጋትን ለማጥፋት እና በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ ተቀራርቦ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም የሀገራቱን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ የሁለቱን ሀገራት እና ህዝቦች ትስስር እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር መስማማታቸው ተጠቅሷል።

በውይይታቸው ለሶማሊያ ሰላም፣ መረጋጋት እና ሀገር ግንባታ መስዋዕትነት ለከፈለው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አድናቆትና ክብርም ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.