Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመላው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የዕርቅ፣ የሰላም የወንድማማችነት እና የአንድነት ባህል ለሆነው የኢሬቻ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ ሲል መልእክት አስተላልፏል።

የኢሬቻ በዓል የክረምቱ ወራት አልፎ እና የውኃው ሙላት ጎድሎ ጥርት ብሎ የሚወርድበት፣ ጎርፉ ሰክኖ የሚጠራበት፣ ውሽንፍሩና ቁሩ ጠፍቶ በውብና በብሩህ ብርሀን የሚደምቅበት፣ አዝመራው የሚያሸትበት፣ እንስሳት የሚቦርቁበት አእዋፍ የሚዘምሩበት በመሆኑ ይህን ሁሉ ላደረገ ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ነው።

የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነት እና የአብሮነት በዓል እንዲሆን ምክር ቤቱ ተመኝቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.