የሀገር ውስጥ ዜና

የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ በተመረጡ መስመሮች ብቻ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል

By Shambel Mihret

September 30, 2022

የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ በተመረጡ መስመሮች ብቻ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በተመረጡ መስመሮች የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

 

የቢሮው መረጃ እንዳመላከተው÷ ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ የአንበሳ፣ የሸገር ድጋፍ ሰጪ እና የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡስ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ይሰጣሉ፡፡

 

በዚህም መሰረት÷ ከአባኪሮስ ዐደባባይ፣ አያት ዐደባባይ፣ ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ፣ ጎሮ ዐደባባይ፣ አዲሱ ገበያ፣ ቁስቋም፣ ሳንሱሲ፣ አየር ጤና ዐደባባይ እና ጀሞ ዐዳባባይ ተሳፋሪዎች የትራንስፖርት አገልገሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡