Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሠራዊት በንጹሃን ላይ ጉዳት ሳያደርስ በከፍተኛ ጥንቃቄ ወታደራዊ አቅሞችን ነጥሎ እርምጃ እየወሰደ ነው – ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሠራዊት በንጹሃን ላይ ጉዳት ሳያደርስ በከፍተኛ ጥንቃቄና የዒላማ ጥራት የህወሓት የሽብር ቡድን ወታደራዊ ዐቅሞች ነጥሎ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።

የሕወሓት የሽብር ቡድን ለሦስተኛ ጊዜ ግጭት መቀስቀሰሱና ጥቃት መፈጸሙ ይታወቃል።

ይህንን የሽብር ቡድኑን ጥቃት ለማስቆም መንግስት የመከላከል እርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል።

ይህንን ጥቃት ለመከላከል የሽብር ቡድኑን ወታደራዊ ዐቅሞች በተመረጠ ሁኔታና በከፍተኛ ጥንቃቄ ዒላማ በማድረግ የመከላከል ተልዕኮውን እየፈጸመ ነው።

የሽብር ቡድኑ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ እንደቆየው ወታደራዊ አቅሙንና አመራሮቹን በዕምነት ቦታዎች፣ በጤና ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ማኅበራዊ አግልግሎት መስጫ ቦታዎችና ሲቪሎች በሚኖሩባቸው ቦታዎች እየደበቀ ይገኛል።

በተጨማሪም የሽብር ቡድኑ የተመድና ሌሎች የሰብአዊ እርዳታ ተቋማት ንብረቶችን ለማጓጓዣነትና ለመሳሪያ ማከማቻነት እየተጠቀመባቸው ይገኛል።

የመከላከያ ሠራዊታችን በንጹሃን ላይ ጉዳት ሳያደርስ በከፍተኛ ጥንቃቄና የዒላማ ጥራት የወታደራዊ አቅሞችን ነጥሎ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

አሁንም ከሰሞኑ በትግራይ ክልል ዓዲ ዳዕሮ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በተመረጡ ዒላማዎች ወታደራዊ ቁሳቁስና ተተኳሾች ያሉበትን ቦታ ዒላማ አድርጎ እርምጃ ወስዷል።

የሽብር ቡድኑ ሕወሓትን ለማገዝ በታሪካዊ ጠላቶቻችን የተላከው አውሮፕላን ተመቶ ከወደቀበት ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ የአየር ክልል በኢትዮጵያ አየር ኃይል ጥብቅ ቁጥጥር ሥር ይገኛል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.