Fana: At a Speed of Life!

“መልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ” 400 ወጣቶችን አሰልጥኖ ወደ ሥራ አስገባ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “መልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ” በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ እና ትምህርታቸውን በተለያየ ምክንያት ያቋረጡ 400 ወጣቶችን በሽያጭ ሠራተኝነት አሰልጥኖ ወደ ሥራ ማስገባቱ ተገለጸ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን፥ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች በተመቻቸላቸው ዕድል በአግባቡ ተጠቅመው አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በማለፍ ለራሳቸው እና ለማኅበረሰቡ የሚጠቅሙ ብቁ ዜጎች እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡

አቶ ንጉሱ ጥላሁን በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ የሥራ ዕድል ፈጠራ አጀንዳ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የግሉ ዘርፍ እና የአጋር አካላትንም ርብርብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡

“መልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ” ባለፉት ሁለት ዓመታት በመዝናኛው ዘርፍ ላይ 15 ሚሊየን ዶላር በመመደብ ለሁለት ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩ ተገልጿል፡፡

በቀጣይም ኢንቨስትመንቱን ወደ 20 ሚሊየን ከፍ ለማድረግ እና የሥራ የሚፈጠርላቸውን ወጣቶች ቁጥር ወደ 3 ሺህ ለማሳደግ ማቀዱ ተነግሯል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርም ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር “ብቃት” የተሰኘ ፕሮግራም ቀርጾ በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርታቸውን በተለያየ ምክንያት ያቋረጡ 14 ሺህ ወጣቶችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ነው አቶ ንጉሡ ያስታወቁት፡፡

ሠልጣኞቹን ከተቋማት ጋር በማስተሳሰር ወደ ሥራ እንደሚሰማሩ መግለጻቸውንም ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.