Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ተገንብቶ ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከ1ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተገንብቶ ሥራ ጀመረ፡፡

ፋብሪካው ባሕርዳር ከተማ ላይ የተገነባ ሲሆን በወር ከ125 ሺህ ኩንታል በላይ የእንሰሳት መኖ ያቀነባብራልም ተብሏል፡፡

ፋብሪካው ምርቱን በቀጥታ ለተጠቃሚው አርሶ አደር ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻልም ከባለድርሻ አካላት ጋር በባሕር ዳር ውይይት ማካሄዱም ነው የተገለጸው፡፡

በክልሉ 18 የሚደርሱ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ቢኖሩም በጥራት ችግርና በማምረት አቅም ክፍተት ምክንያት አብዛኞቹ የሚፈለገውን ያህል አስተዋጽኦ እንዳላበረከቱ ተጠቁሟል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ የተገነባው “ሙሌ መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ” ቸግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ከወዲሁ ተስፋ ተጥሎበታል ነው የተባለው።

በኤም.ኤስ.ኤ ቢዝነስ ቡድን የሙሌ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ባለቤትየሆኑት አቶ ሙሉዓለም አለነ ÷ ፋብሪካው የእንስሳት መኖ እጥረት በመፍታት ምርታማነትን ለማሳደግ የተገነባ ነው ብለዋል።

ፋብሪካው ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩ የተነገረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምርም ከ700 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

የፋብሪካው የግንባታ ሂደት 18 ወራት ፈጅቷልነው የተባለው። ነው የተባለው።፡፡

በቀጣይም የምርት አቅርቦቱን ከሀገር ውስጥ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መታቀዱንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.