Fana: At a Speed of Life!

  የግሸን ደብረ ከርቤ የንግሥ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዘንድሮው ክብረ-በዓል 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ጎብኚዎች መታደማቸውን በደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡

የንግስ በዓሉን የእምነቱ ተከታዮች ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እያከበሩ ነው ተብሏል፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች በዓሉ ላይ ለመታደም የመጡት ምዕመናን÷በዓሉን ያለምንም ችግር እያከበሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በየዓመቱ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ህዝበ ክርስቲያኑ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የጸጥታ አካላት በቅንጅት የሚያከናውኑት ተግባር ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ የሚመጡ ጎብኝዎችን ቁጥር ለማሳደግ የቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየም መስከረም 17 ቀን 2012 ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ከአምባሰል ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.