Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በወጣቶች ችግር-ፈቺ ሥራ ፈጠራ ከተወዳዳሪ ሀገራት ተርታ ተሰለፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በወጣት ችግር- ፈቺ ሥራ ፈጠራ ከ30 ተወዳዳሪ የዓለም ሀገራት አንዷ መሆኗን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።

ቀጣይነት ያለው ትውልድ ግንባታ ዓለም አቀፍ የወጣቶች የፈጠራ ሀሳብ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው ከተወዳደሩት ሁለት ቡድኖች መካከል በሴቶች የተደራጁት በዓለም አቀፉ ውድድር እየተሳተፉ መሆናቸው ተገልጿል።

ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩት ሴቶች፤ በኦክስጂን እጥረት የሚሰቃዩትን ሕፃናት ለመታደግ እና በዚሁ ምክንያት የሚሞቱትን ሕፃናት መጠን ለመቀነስ የሚያግዝ የፈጠራ ሥራ ይዘው መቅረባቸው ተጠቁሟል።

በቀጣዩ ዙር ካለፉት 30 ሀገራት መካከል የኢትዮጵያን ስም በማስጠራታቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውና በቀጣይም መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው መመኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.