Fana: At a Speed of Life!

አዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት አበረታች ነው- ርዕሰ መ/ር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ምርት የሚጨምሩ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ አዴት ግብርና ምርምር ማዕከል እያከናወናቸው የሚገኙ የምርምር ተግባራት መመልከታቸውን አስታውቀዋል።

ማዕከሉ ምርት የሚጨምሩ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶአደሮች ለማቅረብ እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ግብርና የኢኮኖሚያው መሰረት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ለዘርፉ እድገት እና ውጤታማነት ደግሞ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

የምርምር ማዕከላትን ማስፋፋት እና አዲዳስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

አዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ለአርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚችሉ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችና ሌሎች ግብዓቶችን ለማቅረብ እያደረገ ያለው ጥረት ይበልጥ እንዲስፋፋ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.