Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል በሰላማዊ መንገድና በወንድማማችነት እንዲከበር ያደረጉ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል – የአባ ገዳዎች ኅብረት

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአባ ገዳዎች ኅብረት በአዲስ አበባ የተከበረው የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል በሰላማዊ መንገድና በወንድማማችነት እንዲከበር ላደረጉ ሁሉ ምስጋናውን አቀረበ።

የቱለማ አባ ገዳና የአባገዳዎች ኅብረት ጸሐፊ አባ ገዳ ጎበና ሆላ እንዲሁም የኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ዛሬ በተከበረው የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓልና ነገ በሚከበረው የኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ በዓል አከባበር ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ነው።

በከተማዋ የተከበረው የኢሬቻ በዓል ውብ የነበረና የበዓሉ እሴቶች የሆኑትን ሰላምና ወንድማማችነት ያጎላ እንደነበርም ተናግረዋል።

አባ ገዳ ጎበና ሆላ ÷ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረገው ህዝብ፣ ለፌደራል ፣ለአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ፖሊስ ምስጋና አቅርበዋል።

አባ ገዳው ይህ ሰላማዊነት፣ ወንድማማችነትና አብሮነት በቢሾፍቱ በሚከበረው የኢሬቻ ሆረ አርሰዴ እንዲደገም ጥሪ አቅርበዋል።

የኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን ፈይሶ በበኩላቸው ÷ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ የበዓሉን እሴቶችና ሰላማዊነት ያሳየ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የፀጥታ መዋቅሩ፣ ወጣቶችና ህዝቡ በጋራ ለሰሩት መልካም ተግባርም አመስግነዋል።

የአዲስ አበባ ህዝብ እንግዶችን በማስተናገድና ለበዓሉ ድምቀት የተጫወቱት ሚና ትልቅ ነበርም ብለዋል።

ነገ በሚከበረው የሆረ ሀርሰዴ በዓልም ወንድማማችነት፣ እርቅና ሰላም ይንፀባረቅበታል ብለዋል ሀላፊው በሰጡት መግለጫ።

በአሉ በአንድነት መቆም አሸናፊነቱን የሚገልፅ መልዕክት ያስተላለፈ እንደሆነም አክለዋል።

የበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ የውጭና የውስጥ ጠላቶችን የመረበሽ ፍላጎት ያከሸፈ ነው ብለውታል።

የነገው በዓልም የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነት በዓል እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አቶ ሀሴን ጥሪ አቅርበዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.