Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ወግና ባህል ያላቸው ህዝቦች መገኛ ናት – አባገዳ ጎበና ሆላ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ወግና ባህል ያላቸው ህዝቦች መገኛ መሆኗን አባገዳ ጎበና ሆላ ተናገሩ፡፡

በቢሾፍቱ የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል መከበር ጀምሯል፡፡

በበዓሉ የተገኙት አባገዳ ጎበና ሆላ በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ እኛ ኢትዮጵያውያን የራሳችን የሆነ ወግና ባህል ያለን ህዝቦች ነን ፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ደግሞ የራሱ የገዳ ነጸብራቅ የሆነ ኢሬቻ እንዳለውም ነው የገለጹት፡፡

ኢሬቻ ትናንት በሆረ ፊንፊኔ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በተገኙበት በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ መከበሩን አንስተውም ፥ ህዝቡም በሃይማኖት፣ በጾታና በምንም ሳይለይ ምስጋናውን ማቅረቡን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ከቱለማ አባ ገዳ ጽህፈት ቤት ተነስቶ ወደ ሆረ አርሰዴ እየተጓዝን ነው ብለዋል፡፡

ኢሬቻ ብሄር አይለይም ፤ ሃይማኖት አይለይም ፤ ኢሬቻ አቃፊና ሰላም ነው ያሉት አባገዳ ጎበና ሆላ ፥ በዚህም ከጎረቤት ኬኒያ የመጣ ልዑካን ቡድን በዓሉን መታደሙንም ነው የገለጹት፡፡

ከሀገር ውስጥም ከሶማሌ፣ አፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ ፣ ሲዳማ ክልሎች የመጡ የኦሮሞ ወዳጅ ወገኖቻችን ወደ ሆራ አርሰዴ ምስጋና ለማቅረብ አብረውን እየተጓዙ ነውም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም አባገዳ ጎበና ሆላ ሰላም ለኢትዮጵያ ይሁን ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመሰረት አወቀ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.