Fana: At a Speed of Life!

የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻን ለማክበር የበዓሉ ተሳታፊዎች በጉጉት እየጠበቁ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆረ ሀርሰዲ ኢሬቻን ለማክበር የተገኙ የበዓሉ ተሳታፊዎች ቀድመው በበዓሉ ማክበሪያ በመገኘት ጅማሬውን እየተጠባበቁ ነው።

አዳራቸውን በከተማዋ ጎዳናዎች ህብረ ዝማሬዎችን ሲያሰሙ ያደሩ ወጣቶች አሁንም የምስጋና ዜማዎችን በማሰማት ላይ ናቸው።

በሆረ ሀርሰዲ ቀድመው የተገኙ ወጣቶችና ታዳሚዎች አባገዳዎች ደርሰው በዓሉን እስኪያስጀምት ነው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙት።

በቢሾፍቱ የሚገኙ ሆቴሎችና የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ሲሰጡ ማደራቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው ቅኝት ማየት ችሏል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

ምስል በአብርሃም ፈቀደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.