Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደርጓል፡፡

ድጋፉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ ለአባገዳዎች እና ለዞኑ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ የቦረና ዞን የውሃ ችግር በዘላቂነት እንዲፈታ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነው ብለዋል፡

የውሃ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ የህዝብ ጥያቄ በመሰረታዊነት ምላሽ እስኪያገኝ ድረስም፥ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የዕለት ደራሽ ምግብ ማቅረብ እንደሚገባም ነው የገለጹት።

ድጋፉን የተረከቡት የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጃርሶ ቦሩ ፥ በዞኑ በድርቅ ሳቢያ ከ600 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በመጠቆም ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ማቅረባቸውን ነው ኢዜአ የዘገበው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.