የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ሄቦ” እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የየም ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል “ሄቦ”በጥንታዊው አንገሪ ቤተ መንግስት በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል፡፡
የዓመቱ የመጀመሪያ ወር የሚል ትርጉም ያለው “ሄቦ” የብሔረሰቡ ተወላጆች እንዲሁም የፌደራልና ክልል የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት እየተከበረ ነው፡፡
የራሱ የሆነ የቀናትና ወራት ትርጉምና ስያሜ ያለው የየም ልዩ ወረዳ ብሔረሰብ በወርሐ መስከረም አጋማሽ የአዲስ ዓመት ወይንም የዘመን መለወጫ በዓልን ያከብራል፡፡
የተጣላ ካለ ታርቆና ራሱንና አካባቢውን ንፁህ በማድረግ የሚከበር በዓል የሆነው የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ሄቦ የፍቅር በዓል እየተባለ ይጠራል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ብሔረሰቦች እየተሳተፉም ይገኛሉ፡፡
በተመስገን አለባቸው እና ተስፋሁን ከበደ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!