Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባና በቢሾፍቱ ከተማ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የታደሙበት የሆረ-ፊንፊኔና የሆረ-ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ ቅደመ ዝግጅት በማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቅድመ መከላከል ስራን ከሕዝቡ፣ ከኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረትና ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ በሁለቱም ከተሞች የተከበረው በዓል ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ሕዝብ፣ ለኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረትና ለበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እንዲሁም የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡት የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች ግብረ ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

የሀገራችን ጠላቶችና እነርሱ የሚመራቿው አሸባሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በደኅንነታችን ላይ አደጋ ለማድረስ ስለሚጥሩ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ ቀጣይ በሀገራችን የሚከበሩ ሌሎች ሕዝባዊና ሐይማኖታዊ በዓላት ላይም እያሳየ ያለውን ቀና ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.