Fana: At a Speed of Life!

በሀትሪክ የታጀበው የማንቼስተር ደርቢ በሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኧርሊንግ ሃላንድ እና ፊል ፎደን ሀትሪክ የሠሩበት የማንቼስተር ደርቢ በሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ዛሬ በተካሄደ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ማንቼስተር ሲቲ ማንቼስተር ዩናይትድን 6ለ 3 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የማንቼስተር ሲቲን ጎሎች÷ ፊል ፎደን በ8ኛው፣ በ44ኛው እና በ72ኛው ደቂቃ እንዲሁም ኧርሊንግ ሃላንድ በ34፣ 37 እና በ64ኛው ደቂቃ በማስቆጠር ሃትሪክ ሠርተዋል፡፡
የአንድ ከተማ ተቀናቃኞቹ ሲቲ እና ዩናይትድ ባደረጉት ፍልሚያ የማንቼስተር ዩናይትድን ጎሎች አንቶኒ በ56ኛው እና አንቶኒ ማርሻል በ84ኛው እና በ91ኛው ደቂቃ (በፍጹም ቅጣት ምት) አስቆጥረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.