Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሉማሜ ከተማ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
ዛሬ ከደብረማርቆስ ወደ ሸበል በረንታ ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ሉማሜ ከተማ ውስጥ “ደም አፍስ” ከተባለው ቦታ ሲደርስ ከባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ (ባጃጅ) ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው፡፡
አደጋው ከቀኑ 10 ሰዓት አካበቢ መከሰቱን እና በዚህም የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃ አላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.