Fana: At a Speed of Life!

አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ወቅት አሁን መሆኑን ተገንዝቦ ጊዜውን በአግባቡ እንዲጠቀም ዶ/ር ይልቃል ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሶ አደሩ ሳይዘናጋ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ወቅት አሁን መሆኑን ተገንዝቦ ጊዜውን በአግባቡ እንዲጠቀም የአማራ ብሐየራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ዶክተር ይልቃል ከፋለ በምዕራብ ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ አብካ ቀበሌ በአርሶ አደሮች የተዘጋጀውን የተፈጥሮ ማዳበሪያ ጎብኝተዋል።

የአርሶ አደሩ የኑሮ ሁኔታ ሲሻሻልና ሲቀየር እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገር የኢኮኖሚ ሽግግር ለማድረግ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ አዳዲስ አሠራሮችና ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚስፈልግም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የግብርና ኤክስቴሽን ስርዓቱን በማጠናከር አርሶ አደሩ ቴክኖሎጅን እንዲላመድና እንዲተገብር ያስችለዋ ማለታቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

አርሶ አደሩ ሳይዘናጋ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ወቅት አሁን መሆኑን እና ወጭ የማይጠይቅ መሆኑን በመገንዘብ ጊዜውን በአግባቡ እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እያጋጠመ ያለውን ሰው ሠራሽ የማዳበሪያ እጥረት በተፈጥሮ ማዳበሪያ ማካካስ ይቻላል ያሉት ዶክተር ይልቃል÷ ይህም ምርታማነትን ይጨምራል፤ የአፈር ለምነትንም ያሻሽላል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

በአማራ ክልል እስካሁን ድረስ ከ27 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ በአርሶ አደሮች መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.