የሀገር ውስጥ ዜና

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ለመከላከያ ሠራዊት ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያው ድጋፍ አደረገ

By Tamrat Bishaw

October 02, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን በዋግ ግንባር ጠላትን እየተፋለመ ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ ሞኝነት ንብረት በዞኑ ከሚገኙ ከተማ አስተዳደርና ወረዳዎች የተሰበሰበውን 5 ሚሊየን 552 ሺህ 640 ብር ግምት ያለው ድጋፍ አስረክበዋል፡፡

ድጋፉም÷ 376 በጎች እና 145 ፍየሎችን ጨምሮ ምግብ እና ምግብ ነክ ቁሶችን ማካተቱን የሰቆጣ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ የግንባሩ የሎጅስቲክ ንዑስ ክፍል አስተባባሪና የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ይታያል ገላው አሸባሪው ህወሐት እስከሚወገድ የደጀኑ ሕዝብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!