Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል 620 ተፈናቃይ ዜጎችን በዘላቂነት አቋቋመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግሥት ተጨማሪ 620 ተፈናቃይ ዜጎችን በዘላቂነት አቋቋመ።

በዘላቂ የመፍትሄ ስትራቴጂ ፕሮጀክት አማካኝነት የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ በቆሎጂ የተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ ይገኙ የነበሩ ተፈናቃዮችን ነው በዘላቂነት ያቋቋመው።

ተፈናቃዮቹ ወደ ተዘጋጀላቸው የመኖሪያ ስፍራዎች ዛሬ ተወስደዋል።

እስካሁን የክልሉ መንግስት በቀረፀው የዘላቂ መፍትሄ ስትራቴጂ ፕሮጀክት አማካኝነት የዛሬዎቹን ሳይጨምር ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ 78 ሺህ 174 አባወራዎች ማለትም 453 ሺህ 409 ተፈናቃይ ዜጎች ወደ ትውልድ ቦታቸው ተመልሰው የቀደመ ኑሯቸውን እንዲመሩ አድርጓል።

ለ3 ሺህ 29 አባወራዎች ማለትም ለ20 ሺህ 44 ተፈናቃዮች ደግሞ በክልሉ 12 ወረዳዎች በዘላቂነት ማቋቋም ተችሏል።

ዛሬ የተቋቋሙት ዜጎች ክልሉ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየሰራ ካለው ስራዎች አንዱ መሆኑን የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ-ያሲን ሼኽ ኢብራሂም መናገራቸውን ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.